የክልል፣የዞንና የወረዳ የትምህርት አመራሮች እንዲሁም የክልልና የዞን መምህራን ማህበር አመራሮች፣ የክልል ዳይሬክቶሬቶችና የዞን ቡድን መሪዎች እና ሌሉች ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በሚካሄደው የእቅድ አፈፃፀም ግምገማ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) የትምህርት ስርአታችን ባለፍት 6 ወራት በብዙ ችግር ውስጥ በመሆን ትምህርት መጀመር መቻሉን ተናግረዋል።
የትምህርት ዘምኑን ተፈጥሮዊና ሰው ሰራሽ ችግሮች በመቋቋም ውጤታማ ለማድረግ የትምህርት ባለድርሻ አካላት ላደረጉት ጉልህ ሚናም ምስጋና አቅርበዋል።
በእቅድ አፈፁም ግምገማው በግማሽ ዓመቱ የተገኙ መልካም ተሞክሮዎችን በማስፋትና ከችግሮች ትምህርት በመውሰድ ለቀጣይ የትምህርት ዘመን በትኩረት ይሰራል ተብሏል።
የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ያለምንም ችግር በአጭር ጊዜ ተጠናቆ የተማርዎችን ውጤት መገለፁ በመልካም ተግባር እንደሆነ ተነግሯል።