ከመጋቢት 13-27/2013 ዓ.ም በ8 ኮሌጆች ስልጠና እየሰጠ ነው።
በክልሉ ትምህርት ቢሮ የመርሱ ልማት ባለሙያ አቶ ለጋስ አህመዲን በጎንደር መም/ትምህርት ኮሌጅ የስልጠና አስተባባሪ ናቸው ። እንድሳቸው ገለፃ ስልጠናው ሙሉ በሙሉ መምህራን በየትምህርት ቤታቸው በየእለቱ ከሚገጥማቸው ነገር ጋር ተዛምዶ በተግባር ተደግፎ እየተሰጠ ነው። ይህም ሰልጣኞች ስልጠናውን በከፍተኛ ትኩረት እንዲከታተሉት አድርጓቸዋል። በአጠቃላይ ሰልጣኞች ህፃናትን እንዳይሰለቹ በመዝሙር፣በጭዋታ፣ ነገሮችን በመገጣጠምና በመነካካት እንዲስተምሩ፣ከአካባቢያቸው ቁሳቁስ የትምህርት መርጃ መሳሪያ ማዘጋጀት እንዲችሉ፣ የህፃናትን ባህሪ በመለየትና እንደ ባህሪያቸው በመቅረብ ትምህርትን በፍላጎታቸው እንዲከታተሉና ልዩ ፍልጎት ያላቸው ህፃናትን አካቶ በማስተማር ለትምህርት እድል ተጠቃሚ በማድረግ ለመደበኛው ትምህርት ዝግጁ እንዲሆኑ ከማገዙም በላይ የወረዳና የዞን ባልሙያወች ወደ ትምህርት ቤት ሲወርዱ መምህራንን በእውቀት መደገፍ እንዲችሉ፣ ህብረተሰቡም ልጆቹን ወደ ትምህርት ገበታ እንዲልክ
፣ህፃናቱን ለመደበኛ ትምህርት ዝግጁ እንዲሆኑ የሚያስችል ስልጠና ነው ብለዋል። ከማዕ/ጎንደር ዞን አለፋ ወረዳ የምጡት መምህርት ጊዜወርቅ ደስታ እንደገለፁት ስልጠናው እራሳችንን እንደ ህፃናቱ በማድረግ የህፃናቱን ባህሪ በመላበስ በተግባር በማሳየት የተሳተፍንብት በመሆኑ በቀጣይ ህፃናቱን በአግባቡ ለማስተማር ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል። መምህር ባዜ ብሩ ከዳባት ወረዳ የመጡ የስልጠና ተሳታፊ ናቸው እንደሳቸው ገለፃ ስልጠናው ህፃናትን በመዝሙር ፣በጭዋታ በማዝናናት ማስተማር ውጤታማ እንደሚያደርግ ከስልጠናው ተገንዝበናል።ካሉ በኃላ
በአጠቃላይ ስልጠናው ተከታታይነትና ቀጣይነት ያለው ቢሆን የሰልጣኞችን አቅም በማሳደግ የትምህርት ስርዓቱን ውጤታማ ለማድረግ ያግዛል ብለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *