የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የትምህርት ብርሃን ምዘና ከሚያዚያ 17-19/2013 ዓ.ም በክልል በሁሉም አካባቢዎች ለመስጠት የሚያስችል የማስጀመሪያ መርሃ ግብር ከባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በደብረታቦር ከተማ አካሂዷል።
በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሐላፊ ይልቃል ከፋለ/ዶክተር/ ትምህርት ለዜጎች ተደራሽ ማድረግ ግዴታ ቢሆንም በተለይ በታዳጊ ሀገሮች በአቅም ችግር ትምህርትን ለሁሉም ዜጎች ተደራሽ አልተደረገም፡፡
መንግስት ባለፉት ዓመታት የተቀናጀ ተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርት ተግባራዊ ለማድረግ ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት የተጀመረው ስራ ውጤታማ መሆን አልቻለም ብለዋል፡፡

በተግባር ተኮር የጎልማሶች ትምህርትና በተለያዩ የትምህርት አማራጮች ማንበብ፣መፃፍና ማስላት የቻሉ ጎልማሶችን በመመዘን ከ3ኛ ክፍል ጋር አቻ የሆነ የእውቅና ሰርተፍኬት ይሰጣል ያሉት ቢሮ ኃላፊው ለምዘናው ውጤታማነት ሁሉም አካል እንዲረባረብ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በምዘናው የሚያልፉ ጎልማሶችም በቀጣይ ዓመት ለሚጀመረው የጎልማሶች የክህሎት ስልጠና ተሳታፊ እንደሚሆኑ ታውቋል፡፡
ማንበብ፣መፃፍና ማስላት የሚችል ማነኛውም ጎልማሳ ከሚያዚያ 1-15/2013 ዓ.ም በመመዝገብ ለምዘናው እንዲዘጋጁ ቢሮው ጥሪውን ያቀርባል፡፡


+4
<img class="j1lvzwm4" src="data:;base64, ” width=”18″ height=”18″ />
You, Yosef Girma, Getachew Biazen and 160 others
22 Comments
104 Shares
Like
Comment
Share