ኮሌጆች ጥናቱን ያጠኑት በየተቋማቸዉ ሰልጥነው ስራ ላይ የተሰማሩ መምህራን በሙያዊ ብቃታቸው፣ በማስተማር ችሎታቸውና በምዘና ስርዓታቸዉ ያሉበትን ደረጃ ለማወቅ ነዉ፡፡
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ልሳነወርቅ ተስፋሁን በጥናትና ምርምር የተለዩ ችግሮችና የተጠቆሙ የመፍትሄ ሃሳቦች በቀጣይ የቅድመ ስራ ስልጠና የስርዓተ ትምህርት ዝግጅት ለማካሄድ የሚያግዝና የስራ ላይ ስልጠና አቅም ሊጨምር የሚችል መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 
በጥናት ኮንፈረንሱ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ይልቃል ከፋለ /ዶክተር/ ጥናቱ ሁለት አላማዎች እንዳሉት ገልጸዋል፡፡ ኮሌጆች በጥናቱ በተገኙ ግኝቶችና በተጠቆሙ የመፍትሄ ሃሳቦችን በመተግበር የመማር ማስተማር ስራቸዉን አስተካክለዉ ብቃት ያላቸዉን መምህራን ለማፍራት እንደሚያስችላቸው ተናግረዋል፡፡ በሌላ በኩል የቢሮውና የክልሉ አመራር በመምህራን አመራርና ስምሪት ላይ በጥናት የተለዩትን ችግሮች ሃላፊነት ወስዶ ለማስተካከል እንደሚያግዘዉ ገልጸዋል፡፡የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የጥናት አቅራቢ የሆኑት አበበ ድግሴ /ረዳት ፕሮፌሰር/ በጥናት ኮንፈረንሱ በርካታ ልምድ ማግኘታቸውን ገልጸው በቀጣይ የኮሌጃቸዉን የመማር ማስተማር ሁኔታ በጥናት ላይ ተመስርቶ ለማሳደና ለማሻሻል እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡
የደሴ መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጥናት ያቀረቡት ሃሰን ወርቁ /ዶክተር/ ኮሌጃቸው ባካሄደው ጥናት በርካታ ችግሮች መለየታቸዉን ገልጸዉ ከተለዩት ችግሮች መካከል መምህራን የሚጠበቅባቸዉ የሙያ ብቃት ላይ አለመገኘት፣ አልፎ አልፎ በተመረቁበት የትምህርት ዘርፍ ተመድበዉ እያስተማሩ አለመሆኑንና የቅጥር አለመኖር በጥናቱ መለየቱ ተናግረዋል፡፡ በመሆኑም በጥናት የተለዩ ችግሮችን ለመፍታት በጥናትና ምርምሩ የተቀመጡ የመፍትሄ ሃሳቦችን አሰልጣኝ መምህራን፣ ኮሌጆች፣ ትምህርት ቢሮና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት መተግበር ከቻሉ በሂደት ብቁ መምህራንን አስልጥኖ ማውጣት እንደሚቻል አስተያየታቸውን ሰጥተዋል፡፡


በጥናቱ ላይ ያጋጠሙ ችግሮችንና የተሰጡ የመፍትሄ ሃሳቦች ቢሮዉ ለሚመለከተዉ አካል ሁሉ አደርሶ ለማሻሻል እንደሚሰራ የገለጹት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ይልቃል ከፋለ /ዶክተር/ ኮሌጆች በቀጣይም እንዲህ አይነት ጥናቶችን በማካሄድ ሃላፊነታቸዉን እንዲወጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *