ባሕር ዳር፡ ሚያዝያ 22/2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው መረጃ የ2013 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የአዲስ የተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ ከሚያዝያ 21/2013 ዓ.ም ጀምሮ ይፋ መደረጉን አስታውቋል፡፡
ተማሪዎችም ከታች በተገለጸዉ በየነ መረብ መሰረት የተመደቡበትን ተቋም ማወቅ የሚችሉ መሆኑን ገልጿል፡፡
ዩኒቨርሲቲዎችም እስከ ሚያዝያ 30/2013 ዓ.ም ድረስ ተገቢዉን ዝግጅት በማድረግ የቅበላ መርሃ ግብር የሚያሳዉቁ በመሆኑ ተማሪዎችም አስፈላጊዉን ዝግጅት እያደረጉ እንዲቆዩ ሚኒስቴሩ አሳስቧል፡፡
• ዉጤት ለማየት መግቢያ ዌብሳይት፡- https://result.neaea.gov.et/Home/Placement
• ቅሬታ ለማቅረብ መግቢያ ዌብሳይት (በአካል መምጣት አያስፈልግም)፡- https://forms.gle/Jt9L7F2EDDC62YLQ7

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *