የአብክመ ወሳኝ ኩነት ምዝገባ ኤጀንሲ በ2013 በጀት አመት በ11 ከተሞች ለሚማሩ ተማሪዎች የልደት ምዝገባ በማድረግ የልደት የምስክር ወረቀት ለመስጠት እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡
የተማሪዎች የልደት ምዝገባ የሚያካሂዱ ከተሞች ባህርዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ፣ ቻግኒ፣ አምባጊወርጊስ፣ ደብረማርቆስ፣ ደብረብርሃን፣ ወልዲያ፣ ኮምቦልቻ፣ፍኖተ ሰላም እና ገንደዉሃ ከተማ አስተዳደሮች ሲሆኑ በእነዚህ ከተሞች ከግንቦት 16/2013ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት 688,710 ተማሪዎች የልደት የምስክር ወረቀት እንደሚሰጣቸው ከኤጀንሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *