የትምህርት ሚኒስትሩ ጌታሁን መኩሪያ (ዶ/ር ኢንጂ) በትምህርቱ ዘርፍ ቁልፍ ችግር የሆነውን የትምህርት ጥራት ጉድለት ለመፍታት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትሩ ይህን የተናገሩት ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ ለተወጣጡ 21 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን ባበረከቱበት ወቅት ነው።
በአገሪቱ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ባለፉት ሶስት የሪፎር ዓመታት የተለያዩ መሰረታዊ የማሻሻያ ሥራዎች እየተሰሩ መሆኑንም ሚኒስት ተናግረዋል፡፡
የማሻሻያ ሥራዎች ከተደረገባቸው መካከልም ሥርዓተ ትምህርትን ሙሉ በሙሉ የመቀየር፣ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል፣ የትምህርት ቤት ምገባ መርሃ ግብርና የግብረገብ ትምህርት ይገኙባቸዋል፡፡
በተያዘው የትምህርት ዘመን ከ1 ነጥብ 2 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች በትምህርት ቤት ምገባ መርሐ ግብር ተጠቃሚ እንዲሆኑ መደረጉንም ሚኒስትሩ ገልፀዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ከሚማሩት የትምህርት ዓይነት በተጨማሪ በስምንት የሙያ ዘርፎች ዲፕሎማ ይዘው የሚመረቁበት አዲስ የትምህርት ሥርዓት መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡
በቀጣይ አመትም በተለያዩ የአገራችን ክልሎች በሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ የምገባ መርሃ ግብር ተግባራዊ እንደሚደረግ ሚኒስትሩ ጠቁመዋል፡፡
በመድረኩም ሚኒስትሩ ከቂርቆስ ክፍለከተማ ለተወጣጡ 21 የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች ከ2 ሺ በላይ የሚሆኑ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን አበርክተዋል፡፡
በመድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ ከቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር የተውጣጡ ኃላፊዎች፣ የትምህርት አመራሮች፣ የተማሪ ወላጆች፣ ተማሪዎችና ሌሎችም ተጋባዥ እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *