በምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ አስተባባሪነት የከተማና የወረዳው ትምህርት ፅ/ቤት ርዕሳነ መምህራን ፣የስራ ሃላፊዎች ፣አመራሮችና ባለሙያዎች በተገኙበት በሞጣ ከተማ ና በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ የልምድ ልውውጥ ተካሂዷል ፡፡
በልምድ ልውውጡ የተገኙት የምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ስለሽ ተመስገን በትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩን ስራ ለማጠናከር ምቹ የትምህርት አካባቢን በመፍጠር የትምህርት ጥራትና ተደራሽነት ማረጋገጥ የፕሮግራሙ ዓለማ ነው ብለዋል ፡፡
ለአንድ ሃገር ቀጣይነት ትምህርት ወሳኝ ነው ያሉት ሃላፊው ቀጣይም ተማሪዎች ብቁ ተወዳዳሪ ና በወቅታዊ ሃገራዊ ሁኔታ ሳይናጡ ምክንያታዊ ትውልድ ለመፍጠር እንደ መንግስት የ1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን በሁሉም አካባቢ ተደራሽ በማድረግና ጥራትን ለማረጋገጥ በቅንጅት ትኩረት ተሰጦ የሚሰራ መሆኑን ገልፀው ከነችግራችንም ቢሆን የትምህርት ስርዓቱን ለማሻሻል የታዩ ጥንካሬዎችን በማስፋት ና ድክመቶችን ለማረም መድረኩ አስፈላጊ በመሆኑ ተጠናክሮ ይሰራል ነው ያሉት ፡፡
የመማር ማስተማሩ ስራ በተለያዩ ወቅታዊ ችግሮች ተቀዛቅዞ የነበረውን ለማጠናከር ልምድ ልውውጡ አስፈላጊ ነው ያሉት ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባና ትምህር ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ገደሙ መኮነን የትምህርት ቤቶችን ገፅታ በመገንባት የመማር ማስተማሩ ሂደት ምቹ ሳቢና ማራኪ ለማድረግ እየሰራን ነው ፡፡ ለዚህ ማሳያም እውቀት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት ከነበረበት ችግር ወጥቶ ዛሬ ላይ ከተማ አስተዳደሩ ከክለሉ ጋር በመተባበር የተሻለ ገፅታ ላይ ይገኛል ብለዋል ፡፡
ሌላው ይላሉ ሃላፊው የሞጣ አየር ማረፊያ አጠቃላይ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማሳለጥ የአረንጓዴ ልማት ስራም ማሳያ ነው ቀጣይም የትምህርት ጥራትንና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ከአጋር አካላት ጋር አቅደው እንደሚሰሩ ገልፀዋል ፡፡
ተሳታፊዎቹ እንደገለፁትም የትምህርት ጥራትና ተደራሽነትን ለማረጋገጥ ትምህርት ቤቶችን የውጭና የውስጥ ገፅታ በመቀየር ና ከቅድመ መደበኛ የትምህርት አሰጣጥ ጀምሮ የኢትዮጵያን ታሪክ ለተማሪዎች ለማሳወቅ ማዕከል ተከፍቶ በሞጣ ከተማ እውቀት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰራው ስራ ልምድ የምንወስድበት ነው ብለዋል ፡፡
በእለቱም የሞጣ እውቀት ፋና የመጀመሪያ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤትና አየር ማረፊያ አጠቃለይ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ጉብኝት ተካሂዷል
ሞጣ ከተማ ኮሙዩኒኬሽን