ግንቦት 26/2013ዓ.ም
በሰ/ሸዋ ዞን አሳግርት ወረዳ ት/ት ጽ/ቤት በወረዳው በ12ኛ ክፍል በብሄራዊ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎችና አርአያ ለሆኑ ስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር መምህር ሽልማትን አበርክተዋል፡፡ በዘንድሮው አመት እጅግ ፈታኝና አስቸጋሪ በሆነ ወቅት ችግሩን በመቋቋም በወረዳው ከተፈተኑ ተማሪዎች 525 ነጥብ ያመጣችው ተማሪ ኮኮብ ደረጀ የላብቶፕ ሽልማት በማበርከት ሴት ተማሪዎቻችን በቀዳሚነት እየመሩ የሚገኙ በመሆናቸው ሊበረታቱ ይገባቸዋል ተብሏል፡፡ በተጨማሪም 2013ዓ.ም የመጀመሪያ ወሰነ ትምህርት ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ 19 ተማሪዎች የምስጋናና እዉቅና ሽልማት የመስጠት ፕሮግራም ተካሄዷል፡፡
የአሳግርት ወረዳ መንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዩች ፅ/ቤት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *