የተባበሩት መንግስታት የህፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ለህፃናት መማር ማስተማር ስራ የሚያግዙ ልዩ ልዩ የትምህርት መርጃ ቁሳቁሶችና የንጽህና መጠበቂያ ሳሙናና ሳኒታይዘር ድጋፍ አድርጓል፡፡
ድጋፉ በክልሉ ለሚገኙ ለተለያዩ ትምህርት ተቋማት የሚደርስ ሲሆን በተለይ በቅርቡ ግጭት በተከሰተባቸው በሰሜን ሸዋ እና በኦሮሞ ብሔረሰብ አስ/ ዞን በሚገኙ ወረዳዎች ለሚገኙ ትምህርት ቤቶች ድጋፉ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡