በክልል ደረጃ በተሰራው የዞን ዞን ዝውውር
1. 86 የሁለተኛ ዲግሪ መምህራን ካሉበት ዞን ወደ ሌላ ዞን የተዛወሩ ሲሆን 20 የሁለተኛ ዲግሪ መምህራን ባሉበት ዞን የወረዳ ዝውውር አግኝተዋል በአጠቃላይ 105 የሁለተኛ ዲግሪ መምህራን ዝውውር ተሰርቶላቸዋል፡፡
2. 351 የመጀመሪያ ዲግሪ መምህራን ካሉበት ዞን ወደ ሌላ ዞን የተዛወሩ ሲሆን 287 የመጀመሪያ ዲግሪ መምህራን ባሉበት ዞን የወረዳ ዝውውር አግኝተዋል በአጠቃላይ 638 የመጀመሪያ ዲግሪ መምህራን ዝውውር ተሰርቶላቸዋል፡፡
3. 1,564 የዲፕሎማ መምህራን ካሉበት ዞን ወደ ሌላ ዞን የተዛወሩ ሲሆን 1,887 የዲፕሎማ መምህራን ባሉበት ዞን የወረዳ ዝውውር አግኝተዋል በአጠቃላይ 3451 የዲፕሎማ መምህራን ዝውውር ተሰርቶላቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በዲፕሎማ፣ በመጀመሪያ ዲግሪና በ2ኛ ዲግሪ 4194 መምህራን ከዞን ዞን በተሰራው ዝውውር ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡
4. በሶስቱ ከተማ አሰተዳደር ትምህርት መምሪያዎች በጊዚያዊነት ተመድበው የነበሩ 107 የመጀመሪያ ዲግሪ እና 658 የዲፕሎማ መምህራን ቋሚ የዞን ምደባ ተሰርቶላቸዋል፡፡ በድምሩ 4959 መምህራን ዝውውርና ምደባ ተሰርቶላቸዋል፡፡
5. በቀጣይ በክልል ደረጃ የትምህርት ቤት አመራሮች ፣በዞን ደረጃ የሚሰራው የወረዳ ወረዳ እንዲሁም በወረዳ ደረጃ የሚሰራው የትምህርት ቤት ትምህርትቤት ዝውውር ከ30/09/2013 ጀምሮ የሚሰራ ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *