ከመጀመሪያ ደረጃ እስከ ዩኒቭርሲቲ ምሁራንና የትምህርት ባለሙያዎች እየተሳተፉበት የሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት የመማሪያ ማስተማሪያ መፃህፍት ዝግጅት 3ኛ ቀኑን ይዟል፡፡
በዛሬው ውሎው በተለያዩ የትምህርት መስኮች በየትምህርት ክፍሎች መነሻ ጹሁፎች በምሁራን እየቀረቡ በቡድን ጥልቀ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡
በተለይ በ2006 ዓ.ም በአዲስ የተዘጋጀው የቋንቋ ትምህርቶች የመማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍት በጉድልት የታዩን ነጥቦች ነቅሶ በማውጣት ሰፊ ክርክርና ውይይት ተካሂዷል፡፡ የቋንቋ ትምህርት ለሁሉም የትምህርት አይነቶች መነሻ በመሆኑ ውይይቱ ጠንከር ማለቱን ተመልክተናል፡፡ ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች በቀጣይ ቀን አቅጣጫ ለማስቀመጥ በቀጠሮ ተይዟል፡፡
በሌሎች የትምህርት አይነቶችም ተመሳሳይ ውይይቶች ተካሂደዋል፡፡
ከሰዓት በኃላ በነበረው መርሃ ግብር የሁሉም የትምህርት አይነት አዘጋጆች በጋራ ባካሄዱት ውይይት የትምህርት ፍኖተ ካርታ ዋና ዋና ኃሳቦች፣በነባሩ ስርዓተ ትምህርት በተለያዩ ጥናቶች የተገኙ ጉድለቶች ቀርበው ውይይት የተደረገ ሲሆን በቀጣይ የታሪክ ተወቃሽ ላለመሆን ምሁራንና የትምህርት ባለሙያዎች ሰፊ ውይይቶችና ክርክሮች እያካሄዱ ይገኛሉ፡፡
በውይይቱ የተሳተፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ (ዶክተር) በምሁራንና በባለሙያዎች መካከል እየተደረገ ያለው ክርክርና ውይይት የተሻለ ለመስራ በመሆኑ መልካም ነው ብለዋል፡፡
በዚህ መፃህፍት ዝግጅት ግልጽ አቅጣጫ በመያዝ መስራት ይገባናል ያሉት ቢሮ ኃላፊው በተለይ የቋንቋ ትምህርት ለሁሉም መሰረት በመሆኑ አተኩረን እንሰራለን ብለዋል፡፡
በመማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍት አፃፃፍና ዝግጅት ሙያዊ ውይይት ማምሻውን በመካሄድ ላይ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *