በባህርዳር ከተማ በትናንትናው እለት የተጀመረው የአዲሱ መማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍት ዝግጅት በዛሬው ውሎው በምሁራን የተዘጋጁ የመወያያ ሰነዶች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
በመማሪያ ማስተማሪያ መፃህፍት ዝግጅት የአገር በቀል እውቀት ማካተት እና የመማሪያ ማስተማሪያ መፃህፍት በአፍ መፍቻ ቋንቋ ማዘጋጀት በሚቻልበት ሂደት ዙሪያ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በመጡ ምሁራን በዶክተር ፋሲል መራዊና በፕሮፌሰር ዘላለም ልየው ቀርቦ ውይይት ተካሂዶበታል፡፡
ከሰዓት በኋላ በነበረው መርሃ ግብር በተለያዩ ትምህርት መስኮች የመማሪያ ማስተማሪያ መፃህፍት አዘገጃጀት ጽንስ ሀሳቦችና መርሆወች ዙሪያ ለመፃህፍት ዝግጅቱ ያግዛሉ ተባሉ ሙያዊ ውይይቶች በተለያዩ ቡድንኖች ተካሂደዋል፡፡
መርሃ ግብሩ እስከ ሰኔ 10/ 2013 የሚቀጥል ይሆናል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *