ለተከታታይ አምስት ቀናት በመጽሃፍት ዝግጅት ላይ ሲካሄድ የሰነበተው ስልጠና ተጥናቅቋል፡፡
የአማራ ክልል ምሁራን መማክርት ጉባኤ የፕሮጀክት ጽህፈት ቤት ሃላፊ ዶክተር ዳዊት መኮንን የመጽሃፍት ዝግጅትን አስመልክቶ ለአዘጋጆች የተሰጠው ስልጠና በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሃላፊ ይልቃል ከፋለ /ዶክተር/ ቢሮዉ ከምንጊዜውም የተሻለ የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሃፍት እንዲዘጋጁ ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከአማራ ክልል ምሁራን መማክርት ጋር በመነጋገር በመማሪያና ማስተማሪያ መጽሃፍት ዝግጅት ላይ ሚያጋጥሙ ችግሮችን በየጊዜው እየተከታተለ እንደሚፈታም ቃል ገብተዋል፡፡ አዘጋጆችም የተጣለባቸዉን ታሪካዊ አደራ በአግባቡ እንዲወጡም ቢሮ ሃላፊው አሳስበዋል፡፡
የመማሪያና ማስተማሪያ አዘጋጅ ምሁራንም የተጣለባቸዉ ተማሪዎችን፣ መምህራንን፣ ክልላችንንና ሃገራችንን ፍላጎቶች መሰረት ያደረጉ የመማሪያና ማስተማሪያ መጽሃፍት ለማዘጋጀት ቃል ገብተዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau