በክብረ በአሉ የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አገኘሁ ተሻገር፣ በምክትል ርዕሰ መስተዳደር ማዕረግ የማህበራዊ ዘርፍ አስተባባሪና የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ሙሉነሽ አበበ / ዶክተር/፣ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ይልቃል ከፋለ /ዶክተር/፣የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ድረስ ሳህሉ /ዶክተር/ እና ሌሎች የስራ ኃላፊወች ተገኝተዋል ፡፡
በስራ አፈጻጸማቸው የላቀ ዉጤት ያስመዘገቡ መምህራን ፣ ለበርካታ አመታት አገልግሎት ሲሰጡ ቆይተው ጡረታ የወጡ መምህራን፣ አንደኛ ክፍልን ያበቁ መምህራንና የዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ወስደው 600ና በላይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች እውቅናና ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡
የባህርዳር ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ ድረስ ሳህሉ /ዶክተር/ የድህነት መውጫ በሩ እውቀት በመሆኑ መምህራን እያበረከቱ ላለው አበርክቶ እዉቅና መስጠቱ ሌሎችን የሚያበረታታ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር አገርን በአግባቡ ለመስራት ትምህርት ወሳኝ በመሆኑን መምህራንን ማክበር የመንግስት ተቀዳሚ ግዴታ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ ለዚህም በጡረታ የወጡ መምህራን ማክበርና አሁን በስራ ላይ ያሉትን ማበረታታት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል፡፡ መምህራንን በአግባቡ ያልያዘና ያላከበረ አገር ወደፊት መሻገር አይችልም ያሉት ርዕሰ መስተዳደሩ መምህራን በስራቸው ልክ የሚመጥናቸውን እየተከፈላቸዉ እንዳልሆነ መንግስት እንደሚረዳና ችግሩን ለመፍታት እንደሚጥርም ገልጸዋል፡፡
አዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታ በርካታ ችግሮችን ይፈታል ተብሎ እንደሚጠበቅ የገለጹት ርዕሰ መስተዳደሩ የክልሉ መንግስት የስርዓተ ትምህርት ማሻሻያ እያደረገ መሆኑንና የትምህርት መሰረት ልማት ለማሟላት እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡
በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መምህራን በሚጠበቀው ደረጃ እንዲመደቡና የትምህርት ደረጃቸውንና እውቀታቸውን እንዲያሳድጉ የክልሉ መንግስት እንደሚሰራና የትምህርት አስተዳደሩም በእውቀት እንዲመራ እንደሚደረግ ርዕሰ መስተዳደሩ አቶ አገኘሁ ተሻገር ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau