ለመሆኑ ከመምህራን ከተማሪዎች፣ ከትምህርት አመራሩና ባለሙያዎች በዚህ ወቅት ምን ይጠበቃል?
- ከሰኔ 28-02/11/2013 ዓ.ም የሚሰጠዉ የክፍል ፈተና ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፣ ሮስተር በወቅቱ እንዲሰራ ማድረግ፣ ዉጤት ትንተና መስራትና ለሚመለከተው ማድረስ፡፡
- ተማሪዎች፣ መምህራን፣ ወላጆች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ የትምህርት አመራርና ባለሙያዎች የትምህርት ዘመኑ ከመጠናቀቁ በፊት ትምህርት ቤቶችን አረንጓዴ ሳቢና ማራኪ ለማድረግ የአረንጓዴ ልማት የችግኝ ተከላ በትምህርት ቤቶች መትከል፡፡
- መምህራን በሚያስተምሩበት የትምህርት ዓይነት ለሚቀጥለው የትምህርት ዘመን እንዲያቅዱ አቅጣጫ መስጠት ክትትልና ድጋፍ ማድረግ፡፡
- ሁሉም ትምህርት ቤቶች የትምህርት ቤት ማሻሻያ አቅድ ማቀድ መከታተል ይኖርባቸዋል፡፡ እቅዱ ልዩ ፍላጎትን እና ጾታን ያካተተ መሆኑን ማረጋገጥ ይገባል፡፡
- ሁሉም ተማሪዎች በአመቱ መጀመሪያ ከትምህርት ቤት የተዋሱትን መማሪያ መጸሀፍት እንዲመልሱ ማድረግ፡፡
- በትምህርት ቤት ሊሰሩ የሚገቡ የክረምት ስራዎችን የትኩረት ነጥቦች በመለየት ማቀድና መተግበር፡፡
- የ2013 የትምህርት ዘመን የስራ አፈጻጸም ግምገማ በማድረግ ለ2014 የትምህርት ዘመን እቅድ ባለድርሻ አካላትን ባሳተፈ መንገድ ማቀድ፡፡
- መረጃዎችን አደራጂቶ መያዝ መተንተን፣ በግብዐትነት መጠቀም፣ ለሚመለከተዉ አካል ማሳወቅ፡፡