የልምድ ልውውጥ ውይይቱ ያስፈለገበት ምክንያት በትምህርት ዘርፍ የልማት ክዋኔዎች ምክንያት ሊከሰቱ የሚችሉ የአካባቢና ማህበረሰብ ማህበራዊ ደህንነት ላይ ልምድ ካላቸው የሴክተር መስሪያቤት ባለሙያወች ልምድ ለመቅሰም መሆኑን በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የጅኩፕ-ኢ አካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ባለሙያ አቶ ደባሱ ያየህ ገልፀዋል፡፡
የአካባቢና የህብረተሰብ ማህበራዊ ደህንነትን መተግበር በትምህርት ቤቶች ዉስጥና አካባቢ የመጠቀሚያ ጊዜያቸዉ አልፎባቸው የተከማቹ ኬሚካሎች በትምህርት ቤትና በአካባቢው ማህበረሰብ ጉዳት እንዳያደርሱ ለመከላከል ፡፡ የትምህርት ቤቶች መፀዳጃ ቤት ፍሳሾች ጉዳት እንዳያደርሱ ለመከላከል ፡፡ በትምህርት ቤት ግንባታ ወቅት ሊከሰት የሚችል የደን ጭፍጨፋ የአካባቢ ብክለት ለመከላከል ፡፡ ለግንባታ ሰራተኞች የስራ ምቹነት እንዲፈጠር ለማድረግ ፡፡ ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ምቹ የትምህርት ቤት ከባቢ መፍጠር ለማስቻል፡፡ በቀጣይ በትምህርት ዘርፉ ለሚሰሩ የልማት እንቅስቃሴዎች የአካባቢና ማህበራዊ ደህንነት ጉዳት በማያስከትል መልኩ ለማልማትና ለመከላከል እንደሚያስችል ተገልጿል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau