በትምህርት ቤቶቹ ተዘዋውረን ያነጋገርናቸው ተማሪዎችም በኮሮና ቫይረስና በአካባቢው ህግ ማስከበር ሂደት የትምህርት ሂደቱ ቢቋረጥም ከጥር ወር ጀምሮ በትምህርት ቤታቸው መምህራን በኩል የማጠናከሪያ ትምህርት በማግኘታቸው ፈተናውን ለመውሰድ አለመቸገራቸውን ተናግረዋል፡፡
የአላማጣ አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ት/ቤት ርዕሰ መምህር እያሱ ምስጋን ከመደበኛ የስራ ስዓት የማካካሻ ክለሳ በመስጠት ትምህርት እንድሰጥ በመደረጉ ተማሪወቹ ከኩረጃ በፀዳ ሁኔታ እንደፈተኑ ጥረት አደርገናል ብለዋል። የአላማጣ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ በሪሁን አዲሃኖም በከተማው 6 አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መኖራቸውንና 917 ተማሪዎች በ7 የትምህርት ዓይነት የ8ኛ ክፍል ፈተናን እየወሰዱ ነው ብለዋል።
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮና የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ለዛሬው የፈተና ጊዜ መድረስ ላበረከቱት አስተዎፆኦ አመስገነው በቀጣይ መንግስት በጁንታው የተዘረፉና የውስጥ ቁሳቁሳቸው ያልተሟላላቸው ትምህርት ቤቶች መኖራቸውን የደረጃ ዕድገት ጥቅማጥቅም የሚገኙ መምህርን ስላሉ የበጀት ችግር ስላለብን መንግስት ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል፡፡
የሰሜን ወሎ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ አቶ የኋላሽት ልዑልሰገድ በዞኑ በ461 ትምህርት ቤቶች 28 ሺህ 520 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ መሆኑንና በህግ ማስከበር ስራው ነፃ በወጡ አካባቢዎች የመማር ማስተማር ሂደቱን በመደገፍ 2 ሺህ 104 ተማሪዎች ፈተነውን ሰላማዊ በሆነ መልኩ እንዲወስዱ አድርገናል ብለዋል።
መረጃው የሰሜን ወሎ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *