በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከሰኔ 23 _25/2013 ሲሰጥ የሰነበተው የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መጠናቀቁን የክልሉ ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር አቶ ካሴ አባተ ተናግረዋል ፡፡
ፈተናው በ5,521 ትምህርትቤቶች የተሰጠ ሲሆን ሁሉም ባለድርሻ አካላት ባደረጉት ጥረት በሰላም መጠናቀቁን አቶ ካሴ ገልጸዋል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ፈተናው በሰላም እንዲሰጥ ለተጋችሁና ለተባበራችሁ መምህራን፣ ተማሪዎች፣ የጸጥታ አካላት፣ ወላጆችና የትምህርት አመራሮች የላቀ ምስጋናዉን ያቀርባል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau