በአማራ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ትምህርት መምሪያ ከሰኔ 23 ቀን ጀምሮ ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የነበረው የ8 ክፍል ሚኒስትሪ ፈተና በሰላም መጠናቀቁን የመምሪያው ኃላፊ አቶ አይነኩሉ አበበ አስታውቀዋል።
በዛሬው እለት በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ ዱበቱ ትምህርት ቤት የኦሮምኛ የአፍ መፍቻ ቋንቋ ፈተና መሰጠቱንና በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ለ41ሺ 951 ተማሪዎች የተሰጠው ፈተና ተጠናቆ ወደ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤቶች ተጓጉዞ መግባቱን ገልጸዋል።
ፈተናው እስከ ሐምሌ 20 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ በአግባቡ ታርሞ ውጤቱ ለተማሪዎች ይፋ እንደሚሆን የገለጹት ኃላፊው ፈተናው ከቅድመ ዝግጅት ጀምሮ በሰላም እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ ፈተኝ መምህራንና ሱፐቫይዘሮች ፣ በየደረጃው ለሚገኙ የፀጥታ አካላትና ወላጆች ምሥጋና አቅርበዋል።
አቶ አይነኩሉ አያይዘውም ካለፈው ዓመት መልካም አፈጻጸም ተሞክሮ በመውሰድ በተያዘው ክረምት የአረንጓዴ ልማት ሥራችንን በማጠናከር አሻራችንን በማሳረፍ የኢኮኖሚ ተጠቃሚነታችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።
በተመሳሳይ አዳዲስ መማሪያ ክፍሎችን በመገንባት ፣ ነባሮቹን በመጠገንና በማስዋብ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ የማሻሻል እና የገጽታ ግንባታ እንደሚሠራ ጠቁመው የማጠናከሪያ ትምህርት መስጠትና የአረጋዊያን ቤት ጥገና ቁልፍ ተግባሮቻችን ናቸው ብለዋል።
መረጃው የሰሜን ሸዋ ዞን ኮሙኒኬሽን ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau