የትምህርት ዘርፉ ከሴቶች የሚገኝ ጥበብና አስተዋጽኦን በመጠቀም ለውጥ ማምጣት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ጾታና ኤች አይ ቪ / ኤድስ/ ክፍል ባለሙያ የሆኑት አቶ ፈንታሁን ተሰጋ የሴቶች ተሳትፎና ዉሳኔ ሰጭነት በፖሊሲ ፣ ስትራቴጅ፣ ደንብና መመሪያዎች በመኖራቸው ብቻ ማምጣት የማይቻል በመሆኑ ሴቶች በአመለካከት፣ እራስን በማብቃትና እራስን በመሆን ተሳተፏቸውን ሊያሳድጉ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ሴት ሰራተኞች አቅማቸውን በማጎልበት የዉሳኔ ሰጭነት ሚና ኖሯቸው የቢሮውን ራዕይና ተልዕኮ ለማሳካት የሴት ሰራተኞች ሚና ከፍተኛ መሆኑን ገልፀዋል፡፡ ይህ አቅም የማጎልበት ስራ እስከ ትምህርት ቤት ድረስ ለማድረስ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በትምህርት ተሳትፎ ላይ ጾታዊ ምጥጥን ማሳከት የቻለ ቢሆንም ሴቶችን ወደ ትምህርት ዘርፍ አመራርነት ለማምጣት ግን ተግዳሮቶች ገጥመውታል፡፡ በመሆኑም በሴቶች ላይ የሚሰራ የአቅም ማሳደግ ስራ ለሃገር የሚሰራ ስራ በመሆኑ የሴቶችን አቅም ለማሳደግ በትኩረት እንደሚሰራ አቶ ጌታቸው ገልጸዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau