ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘና እና ፈተናዎች ኤጀንሲ የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ከጥቅምት 2014 ዓ.ም አጋማሽ በኋላ እንደሚሰጥ ገለጸ።
በዘንድሮው የትምህርት ዘመን የትግራይ ክልል ተማሪዎችን ሳይጨምር 620 ሺህ ተማሪዎች ተመዝግበው ፈተናውን በመጠባበቅ ላይ ናቸው ተብሏል።
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ዲላሞ ኦቶሬ በሰጡት መግለጫ ኤጀንሲው በማንኛውም ሰዓት ፈተናውን መስጠት የሚያስችል ዝግጅት አድርጓል።
በሀገሪቱ አንዳንድ ትምህርት ቤቶች የኢኮኖሚክስ ትምህርት ባለመሰጠቱ ፈተናው የማይሰጥ መሆኑንም ገልጸዋል።
(ኢዜአ)
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau