የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች ለአማራ ልዩ ሃይል፣ ሚኒሻ፣ የሃገር መከላከያ ሰራዊትና የህልውና ዘመቻ ላይ ለሚሳተፉ የየክልሎች የልዩ ሃይል አባላት ሁሉ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
የቢሮው ሰራተኞችና አመራሮች ዛሬ ደም ለግሰዋል፡፡ በሌላ በኩል የቢሮው ሴት ሰራተኞች በህልውና ዘመቻው ላይ ለሚሳተፉ ጀኞች የስንቅ ዝግጅት በማድረግ ላይ ናቸው፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኞችና አመራሮች ቃል በገቡት መሰረት የአንድ ወር ደመወዛቸውን አንድ ሚሊየን አንድ መቶ ዘጠና አራት ሽህ ሃያ ሰባት ብር ለግሰዋል፡፡
 
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau-106469466135085

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *