በምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ ለ2014 ዓ.ም የትምህርት ዘመን “አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ “በሚል መሪ ሃሳብ ወላጆቻቸውን ላጡ ተማሪዎች ፣ለዘማች የሚሊሻ ልጆችች እና ደብተር ለመግዛት አቅም ለለላቸው ተማሪዎች ግልጋሎት የሚውል የመማሪያ ቁሳቁስ 83 ደርዘን ደብተር እና 6 ባኮ እስክፒርቶ ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የተሰበሰበ መሆኑን የቋራ ወረዳ ሴቶች ወጣቶችና ህፃናት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ አዲሴ ሁነኘው ገልፀዋል።
ኃላፊዋ እንዳሉት ከዚህ ዉስጥ 26 ደርዘን ደብተርና 3 ባኮ እስክፒርቶ በቋራ ወረዳ ሚሊሻ ጽ/ቤት አስተባባሪነት የተሰበሰበ መሆኑን ገልፀዋል።
በመጨረሻም በትምህርት መማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ምክንያት ከትምህርት ገበታቸው እንዳይቀሩ ለማድረግ ደብተር ፣ዕስክፒርቶ በመግዛት ፣ጉልበት ገንዘባቸውን ድጋፍ ለአደረጉ አካላት እና ሴክተር መስሪያ ቤቶች ላቅ ያለ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘገባው የቋራ ኮሚዩኒኬሽን ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *