በምዕራብ ጎጃም ዞን በፍኖተ ሠላም ከተማ 14 በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ማህበራዊ ሚዲያን በመጠቀም ባሰባሰቡት ሐብት ለ308 የዘማች ልጆችና አቅም ለሌላቸው ከሁሉም ቀበሌ ለተመለመሉ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርገዋል ።
ወጣቶቹ በጎ ሐሳብን አንግበው ባለፈው ሐምሌ ወር ጀምረው ተማሪዎች በአቅም ማነስ ምክንያት መማር እየፈለጉ ትምህርት እንዳያቋርጡ በማሰብ የሒሳብ አካውንት በመክፈት በማህበራዊ ሚዲያ ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል ። በማህበራዊ ሚዲያ ባደረጉት ርብርብ በሐገር ውስጥና በውጭ ሀገር የሚገኙ ለጋሹች ባደረጉት ድጋፍ ከ189 ሽህ ብር በላይ መሰብሰብ መቻላቸውን የገለጹት የማህበሩ ጸሐፊ ወጣት አንሙት ታደለ ድጋፉ አቅም ያጡ ልጆችን ችግር የሚያቃልል ነው ብለዋል ።
ከ6ቱ የከተማዋ ቀበሌዎች ለተመለመሉ ከ1-12ኛ ክፍል ላሉ ተማሪዎች 2663 ደብተርና 1500 እስኪርቢቶ የተደረገ ሲሆን ተድጋፉም 97,769 ብር ወጭ ተደርጓል ።
ማህበሩ ለተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ከማሟላት ባሻገር አቅመ ደካሞችን ለማገዝ ዓላማ እንዳለው አብራርተዋል ።
የበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች ሰብሰቢ አቶ ጌትነት ታደሰ ማህበራዊ ሚዲያን ለእኩይ ዓላማ ከማዋል ይልቅ ለማህበረሰቡ የሚጠቅሙ ስራዎችን በመስራት ተጠቃሚ መሆን ይቻላል ይላሉ ። ከተማ አስተዳደሩ የወጣቶች መረዳጃ ማህበር እውቅና በመስጠት ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀዋል ።
የፍኖተ ሠላም ከተማ አስተዳደር ሴቶች ህጻናት ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ጽህፈት ቤት የወጣቶች በጎ ተግባር ሁሉም ሊማርበት የሚገባ ብዙዎችን ተጠቃሚ ያደረገ ነው ። ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች ትምህርታቸው ላይ ትኩረት በማድረግ ውጤታማ እንዲሆኑም አሳስበዋል ።
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪ እጹብድንቅ ተሰማና እና ተማሪ ይከበር አበረ የትምህርት ቁሳቁስ መወደድ በእኛ አቅም ለማሟላት አስቸጋሪ አድርጎት የነበረ ቢሆንም በበጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በመፈታቱ ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል ። እኛም በትምህርታችን ውጤታማ ሁነን የእነሱን አርአያ ለመከተል ዝግጁ ነን ብለዋል ።
መረጃው የፍኖተ ሰላም ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *