ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም ከአራት ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ የቤተ ሙከራና የመማሪያ ክፍሎች አስገንብተው አስረከቡ፡፡
===========================================
የወንቅሸት ገዳምና አምስቱ አድባራት መስራችና አስተዳዳሪ የሆኑት ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም ከአራት ሚሊዬን ብር በላይ በሆነ ወጭ በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ሽሜ ማሪያም የመጀመሪያ ትምህርት ቤት ያስገነቡትን ሁለት ብሎኮች ያሉት ሶስት የቤተ ሙከራ ክፍሎች እና አራት የመማሪያ ክፍሎች አስገንብተው ለህብረተሰቡ አስረክበዋል፡፡
የሽሜ ማሪያም የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት በ 1963 የተመሰረተ ሲሆን ላለፉት 50 አመታት በርካታ ምሁራንን አፍርቷል፡፡ ትምህርት ቤቱ ባለፈው አመት ሃምሳኛ አመቱን ሲያከብር በቦታው የተገኙት ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም የትምህርት ቤቱ ከደረጃ በታች መሆንን ተመልክተው ተጨማሪ ክፍሎችን ለመገንባት ቃል ገብተው ነበር፡፡ ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም በሃምሳ የስራ ቀናት ብቻ አራት የመማሪያ ክፍሎችን፣ ሶስት የቤተ ሙከራ ክፍሎችን ከነሙሉ የመምህራንና የተማሪዎች መቀመጫ ወንበሮች ጋር ገንብተው አስረክበዋል፡፡
የደራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ጀማል ኡመር ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም በወረዳው 23 ኪሎ ሜትር የጠጠር መንገድ በማስገንባት፣ በአንበሳሜ ከተማ ለሚገኘው ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አንድ ብሎክ ባለ አራት መማሪያ ክፍል፣ በአንበሳሜ ከተማ አራት ኪሎ ሜትር የውስጥ ለውስጥ የጠጠር መንገድ በማሰራት በልማት ትልቅ ተሳትፎ ያላቸው አባት መሆናቸውን ገልጸዋል፡፡
ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም በየአመቱ ከ500 በላይ ለሚሆኑ የደረጃ ተማሪዎችና የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪይዎች ደበተር፣ እስክብሪቶና ሌሎች የመማሪያ ቁሳቁስ በማሟላት አርያነት ያለው ተግባር የሚፈጽሙ ትልቅ አባት መሆናቸውንም አቶ ጀመል ኡመር ተናግረዋል፡፡
የደቡብ ጎንደር ዞን ብልጽና ጽህፈት ቤት የፖለተካ ዘርፍ ሃላፊ አቶ ጥላሁን ደጀኔ ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም የሰውን ልጆች ዘር ቀለም ሳይለይ አገልግሎት የሚሰጥ ትምህርት ቤት በመገንባታቸው ክብር ይገባቸዋል ሲሉ ገልጸዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን ትውልድ የሚያድገውና የሚጠቀመዉ ደረጃውን በጠበቀ ትምህርት ቤት ሲማር በመሆኑ ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም ይህን ተረድተው ትምህርት ቤት በመገንባታቸው በህጻናት ስም አመስግነዋል፡፡
ሰይጣንና ድህነት የሰው ልጅ ጠላቶች ናቸው በሚል አባባላቸው የሚታወቁት ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም ሰይጣንን በጸሎት ድህነት ጠንክሮ በመስራት ማሸነፍ እንደሚቻል ገልጸዋል፡፡ ከልጅነታቸው ጀምሮ ሆስፒታል፣ ገዳምና ትምህርት ቤት የመገንባት ህልም እንደነበራቸው የተናገሩት ርእሰ ባህታዊያን ሊቀ አእላፍ ቆሞስ አባ ዮሃንስ ተስፋማሪያም ዛሬ ላይ ማህበረ ትጋት የተሰኘ ማህበርን በማሰተባበር እየሰሩ መሆኑንና ወደፊትም ይህንን ተግባራቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *