የፋርጣ ወረዳ ሴቶች ህፃናት ወጣቶች ጽ/ቤት በጦርነቱ ለተጐዱና የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው ተማሪዎች የመማሪያ ደብተር ድጋፍ አደረገ፡፡
=======================================
የፋርጣ ወረዳ ሴቶች ህፃናትና ወጣቶች ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ብርቄ መርሻ እንደገለፁት በወረዳው እንድርጌ፣ ጋሳይ፣ አውዘትና ሳህርና ቀበሌት በጠትነቱ ለተጐዱና የኢኮኖሚ ችግር ላለባቸው 60 ተማሪዎች 25 ሺ ብር ወጪ በማድረግ 60 ደርዘን ደብተር ለእያንዳንዳቸው አንዳንድ ደርዘን ድጋፍ ድጋፍ መደረጉን ገልጸዋል፡፡
ወ/ሮ ብርቄ አክለው እንደገለፁት ድጋፉ የተገኘው ከፋርጣ ወረዳ ሴቶች፣ ህፃናትና ወጣቶች ጽህፈት ቤት የጥምረት ኮሚቴ ከሰበሰበው ብርና ከሴክተሮች ከተገኘ የቁሳቁስ ድጋፍ ሽያጭ መሆኑን ገለፀዋል፡፡
በመጨረሻም ወ/ሮ ብርቄ የሃገራችን የነገ ተስፋ ለሆኑና በጦርነቱ ለተጐዱና ለችግረኛ ተማሪዎች ሁሉም አካል እገዛ በማድረግ የበኩሉን ድርሻ ሊወጣ ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
መረጃው የፋርጣ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *