አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ ጥሪን የተቀበለው የአማራ ክልል ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሰራተኞቹን በማስተባበርና ከቢሮው በጀት በመመደብ ያሰባሰበውን የደብተርና እስክርቢቶ ለክልሉ ትምህርት ቢሮ አስረከበ፡፡
የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሰራተኞችን በማስተባበርና ከተቋሙ በጀት በመመደብ 410 ደርዘን ደብተርና 51 ፓኮ እስክርቢቶ ዛሬ አስረክቧል፡፡
ድጋፉን ያስረከበቱ የተቋሙ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ደሳለኝ አለምነህ አሸባሪው ቡድን በክልሉ ባደረገው ወረራ በርካታ ተማሪዎች ተፈናቅለዋል፡፡ የተፈናቀሉ ተማሪዎች ትምህርታቸውን እንዳያቋርጡ ቢሮውና ሰራተኞች የድርሻቸውን ለመወጣት ያደረጉት ድጋፍ ነው ብለዋል፡፡
የክልሉ ትምህርት ቢሮውም ድጋፉን የችግሩ ተጋላጭ ለሆኑ ተማዎች በፍጥነት እንዲደርስ የጠየቁት ኃላፊው ሌሎች ተቋማትም ሰራተኞን በማስተባበርና ከተቋማቸው በጀት በመመደብ ተመሳሳይ ድጋፍ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነትና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ጌታቸው ቢያዝን የክልሉ ገንዘብና ኢኮኖሚ ቢሮ ሰራተኞችና ተቋሙ ያደረጉት ድጋፍ በችግር ውስጥ ላሉና የትምህርት ቁሳቁስ ማሟላት ለማይችሉ ተማሪዎች ላደረጉት ድጋፍ በተማሪዎች ስም አመስግነዋል፡፡
አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ ጥሪ ተቀብለው ድጋፍ ያደረጉ ተቋማትን ያመሰገኑት ኃላፊው ሌሎች ተቋማት፣ድርጅቶችና ግለሰቦችም ተመሳሳይ ድጋፎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

