በሲስተር ሙሉሰዉ ያየህይራድ እና በአማራ ልማት ማህበር አስተባባሪነት ከ7 ሺ በላይ የተለያዩ አጋዥ መፅሃፍት ለ5 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተበረከቱ፡፡
————————————————————————————————————————-
በምስራቅ ጎጃም ዞን እነማይ ወረዳ ነዋሪነታቸዉ በሰሜን አሜሪካ በሆነዉ ሲስተር ሙሉሰዉ ያየህይራድ እና በአማራ ልማት ማህበር አማካይነት ከዉጭ ሃገር ወደ አገር ዉስጥ የገቡ 7ሺ 1 መቶ 56 የተለያዩ አጋዥ መፅሃፍት በወረዳዉ ለሚገኙ 5 የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተበርክተዋል፡፡
የወረዳዉ ትምህርት ጽ/ቤት ሃላፊ አቶ ዘላለም ደሴ እንደተናገሩት ድጋፍ የተደረጉት መፅሃፍቶች እንደየትምህርት ቤቶች የተማሪ ብዛት የተከፋፈሉ ሲሆን የመፅሃፍቶቹ የመምህራንና የተማሪዎችን አቅም ማጎልበት ስለሚያስችሉ ለትምህርት ጥራት መምጣት ፋይዳቸዉ ከፍተኛ ነዉ ብለዋል፡፡
የበላይ ዘለቀ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምክትል ርዕሰ መምህር አቶ አስማማዉ ተስፋየ በመፅሃፍት ርክክቡ ወቅት እንደተናገሩት የተደረጋላቸዉ የመፅሃፍት ድጋፍ ትምህርት ቤቱ ያለበትን የአጋዥ መፅሃፍት እጥረት የሚቀርፍ ነዉ ብለዋል፡፡
የበላይ ዘለቀ ከፍተኛ መሰናዶ ትምህርት ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ ጥበቡ ደባስ እንደተናገረዉ የአገር አቀፍ ፈተና ወሳጅ እንደመሆኔ ለትምህርት ቤታችን የተደረገዉ የመፅሃፍት ድጋፍ በተሻለ መልኩ ለፈተና እንድንዘጋጅ የሚያስችልና ተጨማሪ እዉቀት እንድንጨብጥ የሚያስችል ነዉ ብሏል፡፡
ሌላዉ የትምህርት ቤቱ የ10ኛ ክፍል ተማሪ አንተዋ ጌታየ እንደተናገረዉ የተደረገዉ የአጋዥ መፅሃፍት ድጋፍ በትምህርት ቤቱ የነበረዉ የመፅሃፍት እጥረት የሚቀርፍ እና የተማሪዎችን የንባብ ባህል የሚያሳድግ ነዉ ብሏል፡፡
@Enemay communication affairs
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *