የአማራ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ ለተፈናቃይ ተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
—————————————————————–
ቢሮው ለተፈናቃይ ተማሪዎች መማሪያ የሚሆን አንድ መቶ ደርዘን ደብተርና አርባ ፓኮ እስክብሪቶ ለአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አስረክቧል፡፡
ድጋፉን ለትምህርት ቢሮ ያስረከቡት የአማራ ክልል መሬት አስተዳደር ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አወቀ ሲሳይ ድጋፉ ተፈናቃይ ተማሪዎች በመማሪያ ቁሳቁስ እጥረት ከትምህርት ገበታ ውጭ እንዳይሆኑ ለማገዝ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በአሸባሪው የህወሃት ቡድን ወረራ ምክንያት ከአካባቢያቸው ለተፈናቀሉ ተማሪዎች “አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ” በሚል መሪ ቃል የመማሪያ ቁሳቁስ በማሰባሰብ ላይ መሆኑ ይታወሳል፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *