የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ ተፈናቃይ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ መሆኑን አስታወቀ
::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::::
የባህርዳር ከተማ አስተዳደር ትምህርት መምሪያ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ያስተላለፈውን ጥሪ በመቀበል በአሸባሪው ቡድን የተፈናቀሉ ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
በባርዳር ከተማ እስካሁን ባለው መረጃ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች 1354 ተማሪዎች የተቀበለ ሲሆን በ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ 452 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡
በጣና ሀይቅ አጠቃላይ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ትምህርታቸውን ሲከታተሉ ያገኘናቸው ተማሪዎች አሸባሪው ቡድን ከትምህርታችን እና ከመኖሪያ አካባቢያችን ቢነጥለንም የባርዳር ከተማ አስተዳደር ተቀብሎ ትምህርታችን እንድንቀጥል ማድረጉ ምስጋናችን የላቀ ነው ብለዋል፡፡
ከሰቆጣ ከተማ ዋግ ስዩም አድማሱ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመማር ላይ የነበረችውና በአሁ ሰዓት ተፈናቅላ ጣና ሀይቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ትምህርቷን በመከታተል ላይ የምትገኘው ተማሪ ሰሎሜ አበባው አሸባሪው ቡድን ከአላማችን ሊያደናቅፈን አይገባም ብላለች፡፡
የጣና ሀይቅ ትምህርት ቤት ሁሉም የተሟላና ልምድ ያላቸው መምህራን ያሉበት በመሆኑ ትምህርቴን በአግባቡ እየተማርኩ ነው፡፡ ከጓደኞቸ መለየቴ ቢያሳስበኝም አንድ ቀን እንደምንገናኝ ተስፋ አደርጋለሁ ያለችው ተማሪዋ ሌሎች በርካታ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጭ በመሆናቸው መንግስት ተማሪዎች ወደ ትምህርታቸው እንዲመለሱ ሊያደርግ ይገባል ብላለች፡፡
ሌሎች ያነጋገርናቸው ተማሪዎችም የነገ ሀገር ተረካቢ ተማሪዎች ትምህርታችን በሰላም ለመማር ሀገራችን ሰላም እንድትሆን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse