በአማራ ክልል የግዕዝ ትምህርትን ለማስጀመር የሚያስችል ዝግጅት ተጠናቀቀ
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ከባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር የግዕዝ ትምህርትን በክልሉ ለማስጀመር የስርአተ ትምህርት ዝግጅት ስራዎችን ሲሰራ ቀይቷል፡፡
በዘርፉ ምሁራን የተዘጋጀው የስርአተ ትምህርት መጠናቀቁን ተከትሎ የመማሪያና ማስተማሪያ መፀሀፍት ዝግጅት ተደርጓል፡፡
የተዘጋጀው የመማሪያና ማስተማሪያ መፀሀፍት ወደ ሙከራ ከመግባቱ በፊት በዘርፉ ምሁራን ይሁንታ ያገኝ ዘንድ በባህርዳር ከተማ ውይይት ተካሂዷል፡፡
በውይይቱ ግዕዝ ከሚያስተምሩ የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ እንዲሁም ታዋቂ የግዕዝ ምሁራን በተገኙበት ለመማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍቱ ግብአት ያግዛሉ የተባሉ ሀሳቦች ለአዘጋጆቹ ተሰጥተዋል፡፡
የመማሪያና ማስተማሪያ መፃህፍት አዘጋጆችም የተሰጡ ሀሳቦች መፀሀፍቱን ይበልጥ የሚያለጽጉ በመሆናቸው በግብአትነት እንደሚጠቀሙባቸው ተናግረዋል፡፡
በ5ኛ ክፍል ተማሪዎች ይጀመራል የተባለው የግዕዝ ትምህርት በተያዘው የትምህርት ዘመን በተመረጡ ትምህርት ቤቶች የሙከራ ትግበራ እንደሚጀመር ይጠበቃል፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *