አክሮስ አቢሲያ ቱር የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ
አክሮስ አቢሲያ ቱር የተባለ ድርጅት በላይ ጋይንት ወረዳ ንፋስ መውጫ ከተማ ለሚገኙ የአስቻና ንፋስ መውጫ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚማሩ ተማሪዎች በአካል በመገኘት የደብተርና እስክርቢቶ ድጋፍ አደረገ፡፡
ድርጅቱ ለሁለቱ ትምህርት ቤቶች 3ሺህ 720 ደብተርና 3ሺህ 720 እስክርቢቶ ድገፍ ማድረጉን የተናገሩት የድርጅቱ ባለቤት አቶ ፍሬው አየለ ተጨማሪ 1660 ደብተርና እስክርቢቶ በፕላን ኢንተርናሽናል በኩል ለቢሮው እንዲሰጥ ድጋፍ ማድረጋቸውን ባለቤቱ አክለው ገልፀዋል፡፡
ድጋፍ የተደረገላቸው ተማሪዎች በሰ/ወሎ ዞን ተፈናቅለው ለሚማሩ ተማሪዎች፣ለሚሊሻና የፀጥታ ሀይል ቤተሰብ ልጆችና በኢኮኖሚ ዝቅተኛ ለሆኑ ተማሪዎች እንደሆነም ታውቋል፡፡
የአስቻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ር/መምህር አቶ አሰግድ አሰፋ ድርጅቱ ላደረገላቸው ድጋፍ ምስጋና አቅርበው በአስቸጋሪ ወቅት የመጣልን ድጋፍ በመሆኑ ትልቅ ችግር ፈትቶልናል ብለዋል፡፡
አሸባሪው ቡድን በከተማችን በቆየበት ጊዜ የትምህርት ተቋማትን አውድሟል ያሉት ር/መምህሩ የመማር ማስተማሩን ስራ እንዳይቋረጥ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገልን ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡ ሌሎች አካላትም የመማር ማስተማር ስራውን የሚያግዙ ድጋፎችን እንዲያደርጉ ር/መምህሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አንድ ደርዘን ደብተር ለአንድ ተማሪ በሚል መሪ መልዕክት ከልዩ ልዩ ተቋማት፣ድርጅቶች፣ግለሰቦችና ባለሀብቶች ግብአት በማሰባሰብ ላይ መሆኑ ታውቋል፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse