ተማሪዎች የዘማች ቤተሰብ ሰብሎችን እየሰበሰቡ ነው፡፡

_____________________________________________________________

 

በምስራቅ ጎጃም ዞን የደጀን ወረዳ ተማሪዎች የዘማች ቤተሰብ አባላትን ጤፍ ቅድሚያ በመስጠት እያጨዱ ነው፡፡

የተዝካረ ማርያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ የሆኑት ትነበብ ሰናይትና ወርቁ ቁሜ  የሀገራችንን ዳር ድንበር ለማስከበር ቤት ንብረታቸውን ትተው በህልውና ዘመቻው ግንባር የዘመቱ የሚሊሻ አባላትን ሰብል አስቀድሞ በመሰብሰብ ቤተሰቦቻቸው በኢኮኖሚ እንዳይቸገሩና ዘማቾችም ትኩረታቸውን ጠላትን መደምሰስ ላይ እንዲያውሉ እንደሚያግዝ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹ የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል መሰብሰብ ትምህርታቸውን  በማይነካ መልኩ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡

 

ወ/ሮ አበበች ሀረሩ ባለቤታቸው የሃገራቸውን ዳር ድንበር ለማሰከበር በህልዉና ዘመቻዉ ቢሄዱም የአካባቢዉ ማህበረሰብና ተማሪዎች አዝመራዉን በመሰብሰባቸዉ ደስተኛ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

 

በደጀን ወረዳ የተዝካረ ማርያም ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ምናለሰዉ ከፌ ከዚህ ቀደምም ለሕልዉና ዘመቻዉ ከ30ሽህ ብር በላይ ድጋፍ ማድረጋቸዉን አውስተው አሁንም በህልዉና ዘመቻዉ ግንባር ለተሰለፉ የዘማቾች ቤተሰቦችን ሰብል የተማሪዎችን ትምህርት በማይነካ መልኩ እየሰበሰቡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 

በሰብል ስብሰባ ምክንያት የዘማች ቤተሰብ ተማሪዎች  ትምህርታቸዉን እንዳያቋርጡ ሌሎች ትምህርት ቤቶችና ህብረተሰቡም የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብሰብ እገዛ እንዲያደርግ  ርዕሰ መምህሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

 

ለመረጃው የደጀን ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤትን እናመሰናለን፡፡

 

ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w

በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/

በቴሌግራም https://t.me/anrse

 

 

 

 

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *