አሁን ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያስገባ እቅድ ክለሳ በማድረግ የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ እንዲሆን ሊሰራ እንደሚገባ ተገለጸ፡፡
_____________________________________________________
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ክልሉ ካለበት ነባራዊ ሁኔታ አንጻር የተጣጣመ የእቅድ ክለሳ በማድረግ ለዞኖችና ኮሌጆች አስተዋውቋል፡፡
በእቅድ ትውውቁ ወቅት መልእክት ያስተላለፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ማተብ ታፈረ /ዶክተር/ ክልላችን ወረራ የተፈጸመበት ዋና አላማ የልማት ስራዎችን እንዲስተጓጎሉ ታስቦ በመሆኑ የትምህርት አመራሩ፣ መምህራንና የትምህርት ዘርፉ ባለሙያዎች ሁሉ ከችግሩ ከፍ ብለው በመብረር የትምህርት ስርዓቱን በውጤታማነት ሊስቀጥሉ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
የትምህርት አመራሮች የትምህርት ተቋማት እቅድ እንዲያቅዱ በማድረግ፣ አስፈላጊውን የሰው ሃይልና የቁሳቁስ ግብዓት በሟሟላት፣ የአሳላሽና አቋራጭ ተማሪዎችን ቁጥር መቀነስ ላይ ትኩረት ሰጥተው እንዲሰሩ ኃላፊው አሳስበዋል፡፡
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸው ምንም እንኳን ክልላችንና ሃገራችን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑም ነጻ በሆኑ አካባቢዎች በእልህና በቁጭት ስሜት በመነሳሳት የመማር ማስተማር ስራውን በውጤታማነት ለማስቀጠል እንደሚሰሩ አረጋግጠዋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በወራሪው የህወሃት ቡድን የተያዙ አካባቢዎች ነጻ በሚሆኑበት ወቅት ለመምህራንና ተማሪዎች ስነልቦና ድጋፍ በማድረግ፣ የወደሙ ትምህርት ቤቶችንን መልሶ በመገንባት የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር አቅዶ እየሰራ ይገኛል፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *