የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ልዩ ልዩ የመማሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ በአሸባሪው የህውሃት ቡድን ለተፈናቀሉ ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ ልዩ ልዩ የመማሪያ ቁሳቁሶች ድጋፍ አድርጓል፡፡
ቢሮው 156 የተማሪዎች ቦርሳ፣ 250 ደርዘን ደብተርና 54 ፓኮ እርሳስና እስክብሪቶ በአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በኩል ለተማሪዎች እንዲደርስ አስረክቧል፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቢሮ ላደረገው ድጋፍ በተማሪዎች ስም እናመሰግናለን፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse