የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች የዘማች ቤተሰብ ሰብል ሰበሰቡ፡፡
በአማራ ክልል ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስተባባሪነት የአማራ ክልል ትምህርት ቤሮ ሰራተኞችን ጨምሮ የአራት ተቋማት ሰራተኞች የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
በሰብል ስብሰባው የተሳተፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ፣ ሴቶች ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ፣ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ፣ እንዲሁም የስራና ክህሎት ልማት ቢሮ አመራሮችና ሰራተኞች ናቸው፡፡
በሰብል ስብሰባው የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ተገኝቷል።
የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ክብርት ወ/ሮ ፋንቱ ተስፋዬ ውድ ህይወታቸውን ለሀገራቸው ክብር እየሰጡ ላሉ ዘማች ቤተሰቦች ሰብል ለመሰብሰብ የተቋማት ሰራተኞች በመሳተፋቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ወራሪውንና አሸባሪውን የትግራይ ሃይል ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በመደምሰስ ወደ ልማት የምንመለስበትና ኢኮኖሚያችን የምንገነባበት ጊዜ ቅርብ መሆኑን አፈ ጉባኤዋ ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ሴቶች ፣ ህጻናትና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ አስናቁ ድረስ በበኩላቸው መላው የክልላችን ህዝብ፣ አመራሩና የመንግስት ሰራተኛው በገንዘቡ እና በጉልበቱ የተለያዩ ድጋፎችን በማድረግ የኋላ ደጀንነቱን እያረጋገጠ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡ አሁንም አሸባሪው ቡድን ከምድረገጽ እስኪጠፋ ድረስ ህዝቡ ደጀንነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል ኃላፊዋ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በሰብል ስብሰባው የተሳተፉት የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ሰራተኞች የዘማች ቤተሰብ ሰብል ስብሰባ ላይ በመሳተፋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል፡፡
የትምህርት ቢሮ ሰራተኞች አሸባሪውን የህውሃት ቡድን በግንባር እየተፋለሙ ለሚገኙት ለጀግናው የሃገር መከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ሃይል፣ ፋኖና ምሊሻ የገንዘብ ድጋፍ በማድረግ፣ በስንቅ ዝግጅት፣ በደም ልገሳ በማድረግ ደጀንነታቸውን አሳይተዋል፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse