የህልውና ዘመቻዉን ጥሪ ተቀብለዉ በተግባር ያረጋገጡት የሸለል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን የዘማቾችን የደረሰ ሰብል እየሰበሰቡ ነዉ ፡፡
**************
ትምህርት ሚኒሰቴር በሀገር አቀፍ ደረጃ የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የደረሱ ሰብሎችን እንዲሰበስቡ ለአንድ ሳምንት ትምህርት ቤት መዘጋቱን ተከትሎ በምስራቅ ጎጃም ዞን ማቻከል ወረዳ የሚገኘው የሸለል 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችና መምህራን የህልውና ዘማች አርሶ አደሮችን ሰብል ሰብስበዋል፡፡
‹‹ከህልዉናችን የሚቀድም የለም በሚል መሪ ሀሳብ›› ግንባር ለሚገኙ ዘማቾችን የደረሰ ሰብል እየሰበሰቡ ነዉ፡፡ እኛ ትምህርታችንን በሰላም እንድንማር ወራሪዉ፣ ተስፋፊዉ እና ሰዉ በላዉ የትግራይ ቡድን ሙሉ በሙሉ ከምድረ-ገጽ ሊደመሰስ ይገባል ብለዋል፡፡
አሸባሪውን ለመቅበር በጀግንነት ወኔ ወደግንባር በመዝመት ሰላማዊ የመማር ማስተማሩ ስራ እንዲካሄድ አስፈላጊዉን መስዋትነት በመክፈል ላይ ለሚገኙት ዘማቾቻችን ሰብል በመሰብሰብ ላይ መሆናቸዉን ተናግረዋል፡፡
ምንጭ ምስራቅ ጎጃም ኮሙኒኬሽን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ፌስቡክ https: Amhara Education Bureau
ዩቱዩብ Amhara National Regional State Education Bureau
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse