የመራዊ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን የዘማች አርሶ አደር የደረሰ ሰብልን ሲሰበስቡ ውለዋል፡፡
__________________________________________________________________
ከ3ሽህ በላይ የሚሆኑ የመራዊ ሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎችና መምህራን የዘማች አርሶ አደር ቤተሰቦችን ሰብል ሲሰብስቡ ውለዋል፡፡
በሰብል ስብሰባው ወቅት ያነጋገርናቸው ተማሪዎች በደምና በአጥንታቸው ሃገር ለማስከበር የዘመቱ ሚሊሻ አርሶ አደሮችን የደረሱ ሰብሎችን መስብሰባቸው ደስታ እንደፈጠረላቸው ገልጸዋል፡፡
የዘማች አጉማስ ሞላ የትዳር አጋር የሆኑት ወ/ሮ ካሳዬ አለባቸው አራት ቃዳ የዳጉሳና በቆሎ ሰብል የተሰበሰበላቸው መሆኑን ገልጸው ለተማሪዎችና መምህራን ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ጀግናው ባለቤታቸው ሃገሩን ለመጠበቅ የዘመተ በመሆኑ ኩራት እንደሚሰማቸው ወ/ሮ ካሳዬ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የዘማች ልጅ የሆነችው ተማሪ የሻለም አጉማስ ሰብላቸውን ተማሪዎችና መምህራን በህብረት በመሰብሰባቸው ለሰብል ስብሰባ ብላ የምታባከነው ጊዜ ሳይኖር ትምህርቷን በአግባቡ ለመከታተል እንደሚያስችላት ነግራናለች፡፡
በሰሜን ሜጫ ወረዳ ከ17ሽህ በላይ ተማሪዎች፣ መምህራንና የትምህርት አመራሮች የትምህርት ሚኒስቴር በሰጠው አቅጣጫ መሰረት የዘማች ቤተሰቦች ሰብልን ለመሰብሰብ መሰማራታቸውን የሰሜን ሜጫ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ በላይነህ ባዜ ተናግረዋል፡፡
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::