——————————————
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ለአንድ ሳምንት በቆየው ማህበራዊ አገልግሎት ለተሳተፉ ተማሪዎች እና መምህራን ምስጋና አቅርበዋል።
ለሀገራዊ ዘመቻው ውጤታማነት ለአንድ ሳምንት መደበኛ ትምህርት ተዘግቶ ሲሰጥ የነበረው ማህበራዊ አገልግሎት ተጠናቋል።
ለአንድ ሳምንት በቆየው የማህበራዊ አገልግሎትም በመላው ሀገራችን ተማሪዎች እና መምህራን የዘማች ቤተሰቦችን ሰብል በመሰብስብ፣ደም በመለገስ፣ ድጋፍ በማሰባሰብ እና ስንቅ በማዘጋጀት ተሳትፈዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ር) ተማሪዎች እና መምህራን ሀገራዊ ጥሪውን በመቀበል ያደረጉት ንቁ ተሳትፎ የሚደነቅ ነው ብለዋል።ተማሪዎች እና መምህራን ላደረጉት ተሳትፎም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዘመቻው ለሀገሩ እና ወገኑ የሚችለውን ለማድረግ የማይሰስት እና ኢትዮጵያን ወደፊት ለማሻገር ዝግጁ የሆነ ትውልድ መኖሩን ያሳየ ነው ሲሉም ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
በቀጣዩም ለሀገራችን ዘላቂ ሰላምና እድገት ትምህርት ወሳኝ ጉዳይ በመሆኑ በትምህርት ገብታው ተመሳሳይ በሆነ ሀገራዊ ስሜትና ቁርጠኝነት ተግታችሁ እንደምትሰሩ ሙሉ እምነት አለኝ ሲሉም ተናግረዋል።
ተማሪዎችም ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ትምህርታቸውን ጀምረዋል።
መረጃው የትምህርት ሚኒስቴር ነው
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse