“ልጆቼ ኑ ተዋርደናል አገንታችንን ደፍተናል ቤታችን ፈርሷልና በጋራ እንገንባው”
የኮምቦልቻ አጠቃላይ መሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በአማራ ክልል ከሚገኙ በጣት የሚቆጠሩ ደረጃ ሶስት ትምህርት ቤቶች አንዱ ነው፡፡ ትምህርት ቤቱ ባለፉት 45 ከመንግስት፣ ከቀድሞ ተማሪዎቹ፣ ከህብረተሰቡና ከአጋር አካላት ያፈራቸውን በርካታ ሃብትና ንብረቶች በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ዝርፊያና ውድመት ደርሶበታል፡፡
ትምህርት ቤቱ የማንዋልና ድጅታል ቤተ መጽሃፍት፣ የኮምፒውተርና የሳይንስ ቤተ ሙከራዎች ተዘርፈዋል ቀሪዎቹ ጥቅም እንዳይሰጡ ወድመዋል፡፡ ፕላዝማ ቴሌቪዥኖች፣ ጄኔሬተርና ንብረት ክፍል ውስጥ የነበሩ ንብረቶች ተዘርፈዋል፡፡
ወላጆችና ህብረተሰቡ በትብብር በትምህርት ቤቱ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍል ለመገንባት ገንዘብ አዋጥተው ገዝተውት የነበረው የግንባታ እቃዎች በሙሉ ተዝርፈዋል፡፡
በአጠቃላይ ትምህርት ቤቱ እለታዊ የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኝ በመሆኑ መንግስት፣ የቀድሞው ተማሪዎችና ህብረተሰቡ ትብብር እንዲያደርጉላቸው የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ በቀለ ወርቁ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
በኮምቦልቻ አጠቃላይ መሰናዶና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ32 አመታት በላይ ያስተማሩ መምህር አሊ ይማም በትምህርት ቤቱ የፈራችሁ የቀድሞ ልጆቼ ኑ ተዋርደናል አገንታችንን ደፍተናል ቤታችን ፈርሷልና በጋራ እንገንባው ሲሉ እንባ እየተናነቃቸው በተለያዩ የአለማችን ክፍሎች ለሚገኙ የቀደሞው ተማሪዎቻቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በትግራይ አሸባሪና ወራሪ ሃይል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እኔም ድርሻ አለኝ!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *