ኢዱካንስ /EDUkANS/ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት  ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች ድጋፍ አደረገ

ድርጅቱ በደቡብ ጎንደር ዞን በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን ዝርፊያና ውድመት ለደረሰባቸው 10 ትምህርት ቤቶች ከ700 ሽህ ብር በላይ ወጭ የተገዙ የተማሪዎች መቀመጫ ወንበር፣ ሬዲዮኖች፣ የጽህፈት መሳሪያዎችና መጫወቻ ኳሶችን  ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኢዱካንስ ከቁሳቁስ ድጋፉ በተጨማሪ ከበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ ጋር በመተባበር በ10 ትምህርት ቤቶች ለሚይስተምሩ 60 ለተመረጡ መምህራንና የትምህርት ቤት ርዕሰ መምህራን የስነልቦና ድጋፍ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡ እኒህ ስልጠና የወሰዱ መምህራን ተመልሰው ባልደረቦቻቸውን እዲያሰለጥኑ እንደሚደረግም ተገልጿል፡፡

በኢዱካንስ /EDUCANS/ የኢትዮጵያ ሃላፊ አቶ ገዛኸኝ ለሜሳ ድርጅቱ ከዚህ በፊት በአማራ፣ አሮሚያና አፋር ክልሎች ላይ በትምህርት ጥራት ላይ ሲሰራ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡  ድርጅቱ በአማራ ክልል ብቻ ሃምሳ ለሚሆኑ ትምህርት ቤቶች በትምህርት ጥራት ዙሪያ ድጋፍ ሲያደርግ ቆይቷል፡፡ አሁን በተፈጠረው ጦርነት ምክንያት ትምህርትን በአደጋ ጊዜና በኋላ ለማስቀጠል በማሰብ ጉዳት ለደረሰባቸው ትምህርት ቤቶች ድጋፍ መደረጉን ተናግረዋል፡፡ አቶ ገዛኸኝ  የስነ ልቦና ግንባታ ስልጠናው ለመምህራን መሰጠቱ መምህራን ወደ ቀደመ ሰላማዊ አእምሮአቸው በመመለስ የተማሪዎቻቸውን ስነ ልቦና ለማገዝ እንዲያስችል ታስቦ መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡  ድርጅቱ በትምህርትና በስራ ፈጠራ ዙሪያ ለክልሉ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሃላፊው ገልጸዋል፡፡   

ኢዱካንስ /EDUkANS/ የበጌምድር መምህራን ትምህርት ኮሌጅ የትምህርት ተቋማትን ጉዳት አስመልክቶ እርዳታ እንዲያደርግ የቀረበለትን ጥያቄ ተከትሎ  በአፋጣኝ የድጋፍ መልስ መስጠቱ የሚያስመሰግነው መሆኑን የኮሌጁ ዲን አቶ ማስተዋል አሰሙ ገልጸዋል፡፡ ኮሌጃቸው ኢዱካንስ ጋር ለአመታት የቆዬ በትምህርት ጥራት ዙሪያ ሲሰራ የቆዬውን አጋርነቱን አጠናክሮ እንዲቀጥል አቶ ማስተዋል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በደቡብ ጎንደር ዞን ወረራ በፈጸመበት ወቅት በትምህርት ተቋማት ሃብትና ንብረት ላይ ዘረፋና ወድመት መፈጸሙን የደቡብ ጎንደር ዞን ትምህርት መምሪያ ሃላፊ አቶ ደስታ አስራቴ አስታውቀዋል፡፡ ዞኑ ኢዱካንስ ላደረገለት ድጋፍ እያመሰገነ ሌሎች ድርጅቶችም ለትምህርት ተቋማቱ ድጋፍ እንዲያደርጉ መምሪያ ሃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ኢዱካንስ /EDUKNS/  ለትምህርት ቤታቸው ያደረገው ድጋፍ የመማር ማስተማር ስራቸውን ለማከናወን እንደሚያግዛቸው የአስቻ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር አቶ አስግድ አሰፋ ገልጸዋል፡፡

በትግራይ አሸባሪና ወራሪ ሃይል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እኔም ድርሻ አለኝ!!

 

ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::

 

ፌስቡክ https://www.facebook.com/Amhara-Education-Bureau

ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w

በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/Backup dec 2021/Backup dec 2021/

በቴሌግራም https://t.me/anrse

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *