በራያ ቆቦ ወረዳ በሚገኘው የሮቢት 2ኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት 19 የተናጠልና የጅምላ መቃብሮች ተገኙ።
======≠=============
በወረዳው 129 ትምህርት ቤቶች ዘረፋና ውድመት ደርሶባቸዋል።
የራያ ቆቦ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መንገሻ በላይነጋ እንደገለጹት በሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ቅጥር ግቢ ከተገኙት 19 መቃብሮች 3ቱ በእያንዳንዳቸው እስከ 30 ሰዎች የተቀበሩባቸው የጅምላ መቃብሮች ናቸው።
ወራሪው ቡድን የወረዳውን ትምህርት ፅህፈት ቤት እና በወረዳው የሚገኙ 7 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶችን ጨምሮ 129 ትምህርት ቤቶችን በመውረር ዘረፋ መፈጸሙንና ንብረቶችን ማውደሙን ተናግረዋል።
የሽብር ቡድኑ ከዘረፋቸውና ካወደማቸው ንብረቶችና ቁሳቁሶች መካከልም የቤተ ሙከራ ቁሳቁሶች፣ ኮምፒውተሮች፣ ፕላዝማዎች፣ የተማሪ ሰነዶችና ሌሎችም የትምህርት ቤቱ ንብረቶች ይገኙበታል።
የሮቢት 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የጥበቃ ሰራተኞች አቶ ይመር አየለና ዝናቡ ሰማው ወራሪው ቡድን ትምህርት ቤቱን የመቃብር ስፍራ እንዳደረገው ተናግረዋል።
የሮቢት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ባለፈው ዓመት መጨረሻ ከ1ሺ 800 በላይ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምር እንደነበር ተገልጿል።
በትግራይ አሸባሪና ወራሪ ሃይል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እኔም ድርሻ አለኝ!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና የዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *