እነሆ ጀግና
የተማሪዎች መረጃን በማሸሽ ከህወሃት ወራሪ ቡድን ውድመት የታደጉት ግለሰብ፡፡
————————————————-
በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬ ወረዳ ሐይቅ ከተማ ነዋሪ የሆኑት አቶ መሃመድ ኢብራሂም ለሁለት አስርተ አመታት የነበረውን የተማሪዎች የትምህርት ማስረጃ ከወራሪው ቡድን በማሸሽ ከ ውድመት ታድገውታል፡፡
ግለሰቡ ወራሪ ቡድኑ ከመግባቱ በፊት የሀይቅ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ከ1995 እስከ 2013 ዓ.ም ድረስ ያለውን ጠቅላላ የተማሪ መረጃ በአካባቢው በሚገኙ የግለሰብ ቤት በማስቀመጥ በትምህርት ቤቱ የሚማሩ እንዲሁም ከዚህ በፊት የተማሩ ተማሪዎችን መረጃ ከወድመት ታድገዋል፡፡
ግለሰቡ ከዚህም በተጨማሪ የቻሉትን ኮምፒዩተር በማሸሽም ከወራሪ ቡድኑ መታደግ ችለዋል፡፡
አቶ መሃመድ የፈፀሙት ተግባር እጅግ የሚያስመሰግን ሲሆን ትምህርት ቤቱን መልሶ ለመገንባትን የመማር ማስተማር ስራውን ለማስጀመር ሁሉም ድጋፍ በማድረግ የድርሻውን ሊወጣ እንደሚገባ ገልፀዋል፡፡
የህወሃት ወራሪ ሃይል በወረራ በያዛቸው አካባቢዎች በሙሉ የትምህርት ተቋማትን የጦር ካምፕ በማድረግ የቻለውን በመዝረፍ ያልቻለውን በማውደም መረጃዎችን በማቃጠል እንዲሁም የመቃብር ስፍራ በማድረግ ለህዝብ ያለውን ጥላቻ አሳይቷል፡፡
በትግራይ አሸባሪና ወራሪ ሃይል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እኔም ድርሻ አለኝ!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *