የአጣዬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የመማር ማስተማር ስራውን ጀምሯል፡፡
———————————
በህወሃት አሸባሪ ቡድን እና በ ኦነግ ሸኔ ከፍተኛ ገዳት የደረሰበት የአጣዬ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መደበኛ የመማር ማስተማር ስራውን መጀመሩን የ ትምህርት ቤቱ ሱፐርቫይዘር አስታወቁ፡፡
የትምህርት ቤቱ ሱፐርቫይዘር አቶ ማሙሽ ሲከፋኝ ትምህርት ቤቱ አንጋፋና በክልሉ ካሉ ውጤታማ ትምህርት ቤቶች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው ነገር ግን በጥፋት ሀይሎች በተደጋጋሚ የጉዳት ሰለባ በመሆኑ በ ትምህር ቤቱ ላይ ከፍተኛ ውድመት መድረሱን አስታውሰዋል፡፡
የትምህርት አስተዳደሩ በደረሰው ጉዳት ተስፋ ሳይቆርጥ የአጥፊ ቡድኖቹ እቅድ እንዳይሳካ ትምህርት ለማስጀመር ከመምህራን ጋር ተግባብቶ የማስተማር እንቅስቃሴ መጀመራቸውንም ገልፀዋል፡፡
የትምህርት ቤቱ መምህራን በበኩላቸው ካለው ጫና ተላቀው በቀረው ትንሽ የትምህርት ግብዕት የመማር ማስተማር ስራውን በተሻለ የስነልቦና ዝግጅት መጀመራቸውንም ተናግረዋል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የትምህርት ቤቱ መምህራን ትምህርት ቤቱን ከማጽዳት ጀምሮ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ሙሉ በሙሉ እንዲመጡ ስነልቦናቸውን የመገንባት ስራም እየሰሩ ይገኛሉ፡፡
የተለያዩ አካላት ችግሮቹን መጥቶ ከመመልከት በዘለለ የመማር ማስተማር ስራውን ውጤታማ ለማድረግ ከመንግስት ጀምሮ ሁሉም የሚችለውን ድጋፍ እዲደረግ የትምህርት ቤቱ አስተዳደር ጠይቋል፡፡
በትግራይ አሸባሪና ወራሪ ሃይል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እኔም ድርሻ አለኝ!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *