በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ትምህርት ተጀምሯል።
—————————
በህወሓት የሽብር ቡድን ወረራ ምክንያት በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ እና ሀይቅ ከተሞች ከሁለት ወር በላይ ተቋርጦ የቆየው ትምህርት በድጋሚ ተጀምሯል።
በሁለቱም ከተሞች ሙሉ ለሙሉ በሚባል ሁኔታ መደበኛ ትምህርት ተጀምሯል።
የሀይቅ ከተማ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ርዕሰ መምህር ያሬድ ጌታቸው በአሸባሪው ህውሓት ወረራ ምክንያት ሁለት ወር ከ15 ቀን በኃላ በድጋሜ ትምህርት መጀመሩን ገልፀዋል።
ትምህርት ቤቶቹም ባለው ግብዕት መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደትን እያስቀጠሉ እንደሚገኙም ተናግረዋል።
ከ70% በላይ የሚሆኑ ተማሪዎችም በትምህርት ቤቶች ተገኝተው ትምህርታቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።
በትግራይ አሸባሪና ወራሪ ሃይል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እኔም ድርሻ አለኝ!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse