ዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲስ ሴንተር /DEC/ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የ3ሽህ ደብተር ድጋፍ አደረገ
ዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲስ ሴንተር /DEC/ የተሰኘ ግብረሰናይ ድርጅት በጦርነቱ ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች ለሚገኙ ተማሪዎች መማሪያ የሚሆን 3ሽህ ደብተር ድጋፍ አድርጓል፡፡
የድርጅቱ ኤክስኩዩቲቭ ዳይሪክተር አቶ ብርሃኑ ደምሴ ዴቨሎፕመንት ኤክስፐርቲስ ሴንተር /DEC/ ህጻናት ወደ ትምህርት ቤት እንዲመጡ አላማ አድርጎ የሚሰራ በመሆኑ የደብተር ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል፡፡
አቶ ብርሃኑ ድርጅታቸው በጦርነት ጉዳት በደረሰባቸው አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የትምህርትና የጤና ተቋማት መልሶ ግንባታና ለሌሎች ሰብዓዊ ድጋፎች የሚውል 25 ሚሊዬን ብር በጀት በመመደብ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በትግራይ አሸባሪና ወራሪ ሃይል የወደሙ ትምህርት ቤቶችን መልሶ ለመገንባት እኔም ድርሻ አለኝ!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና ዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::