26 የትምህርት ቤት ኮምፒውተሮችን በመደበቅ ከአሸባሪው የህወሓት ኃይሎች ዘረፋ የታደጉት ግለሰብ
**********************
በሰሜን ወሎ መቄት ወረዳ ወቄጣ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አቶ ምስጋን አለቤ የወቄጣ አንደኛ ደረጃ ሙሉ ሳይክል ትምህርት ቤት ንብረት የሆኑ 26 ኮምፒውተሮችን በቤታቸው በመደበቅ ከአሸባሪው የህወሀት ሀይሎች ዘረፋ አድነዋል።
አቶ ምስጋን አለቤ በቤታቸው በርካታ ኮምፒወተሮችን በማስቀመጣቸው የመንግስት ንብረት ለማዳን ደብቀሀል በሚል በአሸባሪው የህወሓት ታጣቂ እንደሚታሰሩና እንደሚገደሉ ማስፈራረያ ቢደርስባቸውም የህዝብ ሀብትን ለዘራፊ አሳልፈው አልሰጡም።።
አቶ ምስጋን አካባቢያቸው ለአምስት ወራት በወረሪው ቡድን ተይዞ የቆየ ቢሆንም መንደራቸውን ባለመልቀቃቸው የትምህርት ቤቱን ንብረት ከአሸባሪው የህወሓት ታጣቂዎች ዝርፊያ እና ውድመት ጠብቀው መቆየታቸውን ኢቢሲ ዘግቧል።
በአሸባሪው የህወሓት ቡድንና ወራሪው የትግራይ ሃይል የተዘረፉና የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እኔም የድርሻዬን እወጣለሁ!!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና የዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse