ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሰችሁ !!
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡
የእናት ሃገራችሁን ጥሪ ተቀብላችሁ ወደ ሃገራችሁ ለገባችሁ መላው የዲያስፖራ አባላትም የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ እንኳን ደህና መጣችሁ ይላል፡፡
ታዋቂው ደቡብ አፍሪካዊ የነጻነት አባት ኒልሰን ማንዴላ “አለምን ለመለወጥ ትልቁ መሳሪያ ትምህርት ነው” የሚል ታዋቂ አባባል አላቸው፡፡ የክልላችን ብሎም የሃገራችን የነገ ተስፋ የሆኑ ህጻናት የወደፊት ህይወታቸውን መሰረት የሚጥሉበት ከ4 ሽህ በላይ ትምህርት ቤቶቻቸን ክፉ መንፈስ በተጠናወተው አሸባሪውና ወራሪው የህወሃት ቡድን ምክንያት ተዝርፈዋል ወድመዋል፡፡
ዛሬ በወረራ ውስጥ በነበሩ የክልላችን አካባቢዎች የሚገኙ ህጻናት ተቀምጠው የሚማሩበት ወንበር፣ ከቴክኖሎጅ ጋር የሚያቆራኛቸው ኮምፒውተር፣ በንደፈ ሃሳብ የተማሩትን ትምህርት በተግባር የሚማሩበት የቤተ ሙከራ ቁሳ ቁስና የሚማሩበት መጽሃፍት የላቸውም፡፡ በዚህም ከአንድ ነጥብ ዘጠኝ ሚሊዮን በላይ ተማሪዎቻችን ከትምህርት ገበታ ውጭ ሆነዋል፡፡
እነዚህ የወደሙና የተዘረፉ የትምህርት ተቋማትን ወደነበሩበት ለመመለስና የመማር ማስተማር ስራውን ለማከናወን በርካታ ሃብት ያስፈልጋል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ የነገ ሃገር ተረካቢ ዜጎችን ለማፍራት በመንግስትና በህብረተሰቡ የተጣለበትን ከባድ ሃላፊነት ለመወጣት ይችል ዘንድ የመላው ህብረተሰብን እገዛ ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም እነዚህን በአሸባሪውና ወራሪው ቡድን የወደሙ የትምህርት ተቋሞቻችን መልሶ በመገንባት፣ የትምህርት ግብአቶችንና የተማሪዎችን መማሪያ ቁሳቁስ በማሟላት ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ገበታቸው ለመመለስ መላው ህብረተሰብ የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ በዓሉ የሰላምና የደስታ እንዲሆንላችሁ በድጋሚ መልካም ምኞቱን ይገልጻል፡፡
በአሸባሪው የህወሓት ቡድንና ወራሪው የትግራይ ሃይል የተዘረፉና የወደሙ የትምህርት ተቋማትን መልሶ ለመገንባት እኔም የድርሻዬን እወጣለሁ!!!
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና የዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *