ሊንክ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምሕርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ።
_____________________________________________________________
ሊንክ ኢትዮጵያ የተሰኘ እና በትምሕርት ላይ ትኩረት አድርጎ የሚሠራ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአማራ ክልል በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ለተጎዱ ትምሕርት ቤቶች ከ2 ነጥብ 8 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት የትምሕርት ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል። ድርጅቱ ድጋፉን ለአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ አስረክቧል፡፡
አሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በአማራ ክልል በፈፀመው ወረራ የሕዝብ አገልግሎት መስጫ ተቋማትን አውድሟል፤ ዘርፏል። ወረራ በተፈፀመባቸው አካባቢዎች በእጅጉ ከተጎዱ ተቋማት መካከል የትምሕርት ተቋማት ናቸው ።
ሊንክ ኢትዮጵያ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት በክልሉ ጉዳት የደረሰባቸውን የትምሕርት ተቋማት ማገዝ የሚያስችል የቁሳቁስ ድጋፍ ዛሬ አስረክቧል። ድጋፉ የተደረገው በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን አስተባባሪነት ነው።
ድጋፉን ያስረከቡት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ንብረት አስተዳዳር ዳይሬክተር ኃይለማርያም አየለ ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ተቋማትን በማስተባበር ጉዳት ለደረሰባቸው አካባቢዎች የሚውል ድጋፍ እያደረገ መሆኑንም ተናግረዋል።
ሊንክ ኢትዮጵያ የተሰኘውን ግብረ ሰናይ ድርጅትም በማስተባበር ከ2 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የትምሕርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጋቸውን ነው የተናገሩት። ድጋፉ ተጠናክሮ እንደሚቀጥም ገልፀዋል። ለወገን ደራሽ መሆናችንን እያስመሰከርን እንቀጥላለንም ነው ያሉት።
ድጋፉን የተረከቡት የአማራ ክልል ትምሕርት ቢሮ የሥርዓተ ትምህርት ዝግጅትና ትግበራ ዳይሬክተር ካሳ አባተ በጦርነቱ ምክንያት ከ1 ነጥብ 9 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምሕርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ገልፀዋል። ተማሪዎችን ወደ ትምሕርት ቤት ለመመለስ በሚደረገው ጥረት ተቋማት ድጋፍ እያደረጉ መሆናቸውን ተናግረዋል።
ሊንክ ኢትዮጵያ ያደረገው ድጋፍ በአስቸኳይ የሚያስፈልጉ ቁሳቁስ መሆናቸውን ነው የተናገሩት። ሌሎች ተቋማትም ድጋፍ እንዲያደርጉ ነው የጠየቁት።
ከአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተጨማሪ መረጃዎችን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያና የዌብ ሳይት አማራጮች ለማግኘት ቀጣዮቹን ሊንኮች ይጠቀሙ ::
ፌስቡክ Amhara-Education-Bureau
ዩቱዩብ UCARNQWN5bm5z2JmKsC_Cn8w
በዌብሳይት https://www.anrseb.gov.et/
በቴሌግራም https://t.me/anrse